ህብረተሰቡ የደመራና የመስቀል በዓልን በሰላም እንዲያከብር አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጓል-የክልሉ ፖሊስ - ኢዜአ አማርኛ
ህብረተሰቡ የደመራና የመስቀል በዓልን በሰላም እንዲያከብር አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጓል-የክልሉ ፖሊስ
ጋምቤላ መስከረም 15/2015 (ኢዜአ) በጋምቤላ ክልል ህብረተሰቡ የደመራና የመስቀል በዓልን በሰላም እንዲያከብር አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሰናይ አኩዎር ዛሬ ለአዜአ እንደገለጹት ነገ እና ከነገ በስትያ የሚከበረውን የደመራና የመስቀል በዓል ህብረተሰቡ በሰላም እንዲያከብር አስፈላጊው ዝግጅት አድርጓል።
የክልሉ የፀጥታ ምክር ቤት ስለ ደመራ በዓሉ እቅድ በማዘጋጀት ከዛሬ ጀምሮ በክልሉ በሁሉም አካባቢ የክልልና ፌዴራል ፖሊስ የፀጥታ አካላት ስምሪት መደረጉን ተናግረዋል።
ከክልል እስከ ወረዳ ባሉት መዋቅሮች ስምሪቱን የሚከታተል ግብረ ኃይል ተደራጅቶ ወደ ስራ መገባቱንም አስታውቀዋል።
ህብረተሰቡ ለፀጥታ ስጋት የሚሆኑ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙት በአቅራቢያው ለሚገኙ የፀጥታ አካላት በማሳወቅ ትብብር እንደያደርግ ኮሚሽነሩ አሳስበዋል።