ስለኢትዮጵያ ክብር በግንባር መስዋእትነት እየከፈሉ ላሉ ጀግኖች ቤተሰቦች የማዕድ ማጋራት መርሃ-ግብር ተከናወነ

20

መስከረም 15 / 2015 (ኢዜአ) ዛሬ ከቤተሰቦቻቸው ርቀው ስለኢትዮጵያ ክብር ስለ ሁላችን ሰላም በግንባር መስዋእትነት እየከፈሉ ለሚገኙ እንቁ ጀግኖች ቤተሰቦች የማእድ ማጋራት መርሃ-ግብር መከናወኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

የማእድ ማጋራት ተግባሩ በሰላም ሰራዊት አባላት አማካኝነት የተከናወነ መሆኑንም ከንቲባ አዳነች በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተካፍለን፣ ተረዳድተን፣ ተሳስበንና ተከባብረን ስንኖር ኢትዮጵያ ከፍ ትላለች ብለዋል።

በተጨማሪም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ከዚህ ቀደም የእሳት አደጋ ደርሶባቸው የነበሩ 9 ቤቶችን በኢንጂነር ጃገማ ቀነኒ አማካኝነት ተገንብተው ዛሬ ለነዋሪዎቹ ማስተላለፍ ችለናል ብለዋል፡፡

በዓሉን ጀግኖቻችንንና ቤተሰቦቻቸውን በማስታወስና በመደገፍ፣ የተቸገሩትን በማገዝ፣ በጎነትን በማጠናከር በአብሮነት እናሳልፍ ነው ያሉት።

በዓሉን ጀግኖቻችንንና ቤተሰቦቻቸውን በማስታወስና በመደገፍ፣ የተቸገሩትን በማገዝ፣ በጎነትን በማጠናከር በአብሮነት እናሳልፍ ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም