በመስቀል አደባባይ የሚከበረውን የደመራ በአል ምክንያት በማድረግ በአሉ የሚካሄድበት ስፍራ የማፅዳት መርሀ ግብር ተከናወነ - ኢዜአ አማርኛ
በመስቀል አደባባይ የሚከበረውን የደመራ በአል ምክንያት በማድረግ በአሉ የሚካሄድበት ስፍራ የማፅዳት መርሀ ግብር ተከናወነ
መስከረም 15 /2015 (ኢዜአ)በመስቀል አደባባይ ከፊታችን የሚከበረውን የደመራ በአል ምክንያት በማድረግ በአሉ የሚካሄድበት ስፍራ የማፅዳት መርሀ ግብር ተከናውኗል።
በተካሄደው የፅዳት ዘመቻም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣የተለያየ እምነት ተከታይ የሆኑ ሃይማኖት አባቶች፣ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና ሌሎች የመዲናዋ ነዋሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል።
የፅዳት ዘመቻው የተለያዩ እምነት ተከታዮች አብሮኘታቸውን ለማሳየት እና መልካም ምኞታቸውን እንዲገልፁ መርሀ ግብሩ እንደተዘጋጀ ተጠቁሟል ።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በየዓመቱ በመስከረም 17 ወር የመስቀል ደመራ በዓልን በተለያዪ ሃይማኖታዊ ሁነቶች በመስቀል አደባባይ ታከብራለች።
በበአሉም ላይ የሃይማኖት አባቶች ምዕምናን እና ሌሎች እንግዶች እንደሚገኙ ይታወቃል ።