የኢትዮጵያና ሱዳን የወዳጅነት ጨዋታ 1 ለ 1 ተጠናቀቀ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያና ሱዳን የወዳጅነት ጨዋታ 1 ለ 1 ተጠናቀቀ

መስከረም 13 /2015 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን(ዋልያዎቹ) ከሱዳን አቻው ጋር ባደረገው የወዳጅነት ጨዋታ 1 ለ 1 በሆነ የአቻ ውጤት ተለያይቷል።
በአበበ በቂላ ስታዲየም በተደረገው የሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ ዋልያዎቹ ለግብጹ ኤል-ጉና ክለብ የሚጫወተው ሽመልስ በቀለ በ31ኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ግብ መሪ መሆን ችለው ነበር።
ከእረፍት መልስ አብዱራዚግ ያዕቆብ በ63ኛው ደቂቃ ያስቆጠረው ግብ ሱዳንን አቻ አድርጋለች።
ኢንተርናሽናል ዳኛ ቴዎድሮስ ምትኩ ጨዋታውን በመሐል ዳኝነት መርተዋል።
ኢትዮጵያና ሱዳን ሁለተኛ የወዳጅነት ጨዋታቸውን ሰኞ መስከረም 16 ቀን 2015 ዓ.ም በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ያደርጋሉ።