በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የኦሞ እና የከፋ ዞኖች ለሰራዊቱ ከ38 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አደረጉ

156

መስከረም 13/2015 (ኢዜአ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የኦሞ እና ከፋ ዞኖች ለሀገር መከላከያ ሰራዊቱ ከ38 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የገንዘብና የአይነት ድጋፍ አደረጉ፡፡

የከፋ ዞን ከ31 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብና የአይነት ድጋፍ ያደረገ ሲሆን፤ድጋፋን የዞኑ የመንግስት ተጠሪ አቶ አስረስ አስፋው ለመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሊውጂ አሰረክበዋል።

የምዕራብ ኦሞ ዞን ደግሞ ከ 6 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የአይነትና የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡

በቀጣይም ድጋፉን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ነው የገለጹት፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም