ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከመንግስታቱ ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ ዋና ሃላፊ ማርቲን ግሪፊትስ ጋር ተወያዩ

42

መስከረም 12 /2015 (ኢዜአ)ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን በኒውዮርክ እየተካሄደ ከሚገኘው 77ኛው የመንግስታቱ ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ጎን ለጎን ከመንግስታቱ ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ ዋና ሃላፊ ማርቲን ግሪፊትስ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም ቢሮው በኢትዮጵያ ሰብአዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች እያደረገ ያለውን ድጋፍ ማሳደግ እንዳለበት አቶ ደመቀ ገልፀውላቸዋል።

ማርቲን ግሪፊትስ በበኩላቸው የመንግስታቱ ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር አብሮ በትብብር የመስራት ፍላጎት እንዳለው መግለፁን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም