በአንድነት ከመከላከያ ሰራዊትና ከሌሎች የጸጥታ ሀይሎች ጎን በመሆን አሸባሪዎች እንመክታለን - የኢሉባቦር ዞን ነዋሪዎች - ኢዜአ አማርኛ
በአንድነት ከመከላከያ ሰራዊትና ከሌሎች የጸጥታ ሀይሎች ጎን በመሆን አሸባሪዎች እንመክታለን - የኢሉባቦር ዞን ነዋሪዎች
መቱ መስከረም 12/2015 (ኢዜአ) በአንድነት ከመከላከያ ሰራዊትና ከሌሎች የጸጥታ ሀይሎች ጎን በመሆን አሸባሪዎች እንመክታለን ሲሉ የኢሉባቦር ዞን ነዋሪዎች ተናገሩ።
ነዋሪዎቹ አሻባሪውንና ተላላኪውን ከመመከት ጎን ለጎን የልማት ስራቸውንም ለማጠናከር ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በዞኑ ከሁሉም ወረዳዎች የተወጣጡ የሕብረተሰብ ክፍሎች አሸባሪዎቹ ሕወሓትና ሸኔ መመከትና የተጀመሩ ልማቶችን አጠናክሮ ማስቀጠል ላይ ያተኮረ ውይይት በመቱ ከተማ ተካሂዷል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች በዞኑ አንዳንድ ወረዳዎች የገባውን ሸኔን ለማጥፋት በሚደረገው ትግልም ከፀጥታ አካላት ጎን ሆነው የሚጠበቅባቸውን እንደሚወጡ ነው የገለፁት።
ከታሳታፊዎቹ መካከል አቶ መሐመድጣሂር አባገሮ "አባቶቻችን ወራሪውን የፋሺስት ጣሊያን ጦር ያሸነፉበትና የሀገራችንን ነፃነት አሰጠብቀው ለእኛ ያስረከቡበትን አንድነታችንን ዛሬም እንደዋነኛ መሳሪያችን መጠቀም አለብን" ብለዋል።
"ሁላችንም አከባቢያችንን ከአሸባሪዎች ለማፅዳት የሚሰራውን ስራ በግምባር ቀደምነት መሳተፍ አለብን" ብለዋል።
በዚህ ወቅት መከፋፈልን በማስወገድ በተባበረ ክንድና በተጠናከረ አንድነት ሰላምን ለማረጋገጥ በጋራ መቆም ግዴታ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ ሌላው የውይይቱ ተሳታፊ አቶ ተካ እንድሪስ ናቸው።
አቶ ተካ "ሁላችንም በምንችለው ሁሉ ከመከላከያ ሰራዊቱ ጎን በመሆን በደጀንነት መሳተፍ አለብን" ሲሉም ተናግረዋል።
አሸባሪው ሕወሓት ሸኔን የፈጠረው ኦሮሞን ሊዘርፍበትና ስሙን ሊያጠለሽበት የፈጠረው ቡድን መሆኑን አንስተው ሽብርተኞቹን ለማጥፋት በሚደረገዉም ትግል ማንኛውንም አስተዋፅኦ ለማበርከት ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል።
በሌላ በኩል የዞኑ ነዋሪዎች የልማት ስራዎች ሳይቋረጡ እንዲቀጥሉ ጠንክረው እንደሚሰሩም ተናግረዋል።
በውይይት መድረኩ ተሳታፊ የነበሩት በኦሮሚያ ልዩ ኃይል የኢሉባቦር ዞን አዛዥ ኮማንደር ዑመር አቡበክር በበኩላቸው "የዞኑ ሕዝብ ከፀጥታ አካላት ጎን በመቆም የዞኑን ሰላም ለማረጋገጥ ጠንክሮ መስራት አለበት" ብለዋል።
ሕዝቡ አንድነቱን ማጠናከር፣ በልማት ስራዎች ላይ ጠንክሮ በመሳተፍ ለአገር አሌኝታነቱን ማሳየት አለበት ነው ያሉት።
በዞኑ የሚገኝም የጸጥታ ሀይል ሕዝቡን እያስተባበረ አሸባሪዎች ላይ የሚወስደው እርምጃ የሚጠናከር ይሆናል ብለዋል።
የኢሉባቢር ዞን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳልካቸው ተፈሪ የዞኑ ሕዝብ አንድነቱን በማጠናከር ከጸጥታ ሀይሎች ጎን እንዲቆም ጠይቀዋል።
ሁሉም ዜጎች ያለአንዳች ልዩነት እነዚህን ጠላቶች ለመመከት በሚደረገው ትግል በጋራ መቆም አለባቸው ሲሉም አሳስበዋል።
የዞኑ ሕዝብ በዚህ ጊዜ የሚጠበቅበትን ሁሉ በመወጣት ለዞኑ ሰላም መረጋገጥ የድርሻውን ማበርከት አለባቸውም ብለዋል።
ሕዝቡ የሀገር ሕልውናን ለማረጋገጥ ከፍተኛ መስዋዕትነት እየከፈለ ላለው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ጎን ሁሉም በሚችሉም የሚችለውን እንዲያደርግ።