የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የአይነት ድጋፍ አደረገ

108

መስከረም 12 /2015 (ኢዜአ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የአይነት ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፉን ከተማ አስተዳደሩን ወክለው የተገኙት የገቢዎች ቢሮ ሃላፊ አቶ ሙሉጌታ ተፈራ ለመከላከያ ሚኒስቴር የፋይናንስ ዳይሬክተር ብርጋዴር ጀኔራል ዘላለም ፈተና አስረክበዋል፡፡

አቶ ሙሉጌታ እንዳሉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሰራዊቱ ድጋፍ ሲያደርግ የዛሬው ለሶስተኛ ጊዜ መሆኑን ጠቅሰው የሀገርን ህልውና ለማስጠበቅ ለሚከፈለው ዋጋ አጋርነትን ለመግለጽ ነው።

ድጋፉ ከክፍለ ከተሞች መሰበሰቡን ጠቅሰው፤ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

በመከላከያ ሚኒስቴር የፋይናንስ ዳይሬክተር ብርጋዴር ጀኔራል ዘላለም ፈተና በበኩላቸው የተደረገው ድጋፍ የህዝብን ደጀንነት እንደሚያሳይና ለሰራዊቱ ትልቅ የሞራል ስንቅ እንደሚሆን አስረድተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም