በዞኖቹ እገዛ ለሚሹ ተማሪዎች የተለያዩ የትምህርት መገልገያዎች ድጋፍ ተደረገ - ኢዜአ አማርኛ
በዞኖቹ እገዛ ለሚሹ ተማሪዎች የተለያዩ የትምህርት መገልገያዎች ድጋፍ ተደረገ
ነገሌ/ጭሮ/ጊምቢ መስከረም 12/2015 በቦረና ፣ ምዕራብ ሀረርጌና በምራብ ወለጋ ዞኖች እገዛ ለሚሹ ተማሪዎች የተለያዩ የትምህርት መገልገያዎች ድጋፍ ተደረገ።
በቦረና ዞን በድርቅ በተጎዱ 3 ወረዳዎች 6 መቶ ተማሪዎች 400 ሺህ ብር ግምት ያለው የተለያየ አይነት የትምህርት ቁሳቁስ ነው ድጋፍ የተደረገው።
የዞኑ ሴቶችና ሕጻናት ፅህፈት ቤት ሀላፊ ወይዘሮ አለሚቱ ቃምጴ ድጋፎቹ በዋናነት ደብተር፣ እርሳስና እስኪርቢቶ፣ ቦርሳዎችና ልዩ ልዩ የስፖርት ትጥቆች፣ የንጽህና መጠበቂያዎችን ያካተቱ ናቸው ብለዋል፡፡
ጽህፈት ቤቱ ቁሳቁሶቹን ለመግዛት የገንዘብ ድጋፉን የሰባሰበው ከበጎ ፈቃደኛ መንግስት ሰራተኞች፣ መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶችና ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
ከዚህም ጎን ለጎን ለመከላከያ ሰራዊት በዞኑ ሴቶች የሚደረገው የአይነትና የገንዘብ ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠሉም ተመልክቷል፡፡
እስካሁንም የዞኑ ሴቶች ከ950 ሺህ ብር በላይ ግምት ያለው 33 ኩንታል ስንቅና 450 ሺህ ብር ጥሬ ገንዘብ ወደ ግንባር መላኩን ጠቅሰዋል፡፡
በተመሳሳይ ምዕራብ ሀረርጌ ዞን ጭሮ ከተማም በዝቅተኛ ገቢ ላለቸው ወላጆች ልጆች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል።
የጭሮ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ አስአና መሀመድ በዝቅተኛ ለሚተዳደሩ ከ6 መቶ በላይ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስና አልባሳት ድጋፍ ተደርጓል ብለዋል፡፡
ድጋፉም ደብተርና እስክሪፕቶ፣ አልባሳትና ሌሎች ለትምህርት አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶች መሆኑን አክለዋል።
ድጋፉ የተደረገላቸው ተማሪዎችም ድጋፉ ጠንክረው ትምህርታቸውን እንደሚማሩ የሚያስችላቸው መሆኑን ተናግረዋል።
ለተደረገላቸውም ድጋፍ ምስጋና አቅርበው መሰል ድጋፎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።
በምራብ ወለጋ ዞንም በክረምት በጐ ፈቃድ አገልግሎትአማካኝነት ዝቅተኛ ገቢ ላለቸው ወላጆች ልጆች የተለያዩ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉ ተገለጿል፡፡
የዞኑ የሴቶችና ዕጸናት ጽዕፈት ቤት ሃለፊ ወይዘሮ ጸሓይነሽ ሔቢሳ እንደተናገሩት በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የተለያዩ በልድረሸ አካለትን በማሳተፍ ድጋፉ ተሰባስቧል።
የተደረገው ደጋፍም የትምህርት ቁሳቁሶች፣ የትምህርት ደምብ ልብስ፣ የተለያዩ አልባሳት፣ የምግብ እህልና ለሎች ድጋፎች ይገኙበታል ብለዋል፡፡
ኃላፊዋ በዞኑ የሚኖሩ በለሃብቶችን፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና የተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎችና ለሎች ተቋማት ላደረጉት ድጋፍም አመስግነዋል፡፡