ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአውሮፕላን "ኢንሱሌሽን ብላንኬት" ማምረቻ ፋብሪካ አስመረቀ

መስከረም 11 ቀን 2015 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ6 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር በላይ ወጪ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ያስገነባውን የአውሮፕላን "ኢንሱሌሽን ብላንኬት" ማምረቻ ፋብሪካ አስመርቋል።

'ኢንሱሌሽን ብላንኬት' አውሮፕላኑ ከፍታውን እየጨመረ በሚሄድበት ወቅት የበረራ አስተናጋጆችና መንገዶኞችን ከከፍተኛ ቅዝቃዜና ከሞተር ድምፅ የሚከላከል ነው።

ፋብሪካው በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ቅጥር ግቢ የተገነባ ነው።

በምርቃት መርሃግብሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው ፣ በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር አጎስቲኖ ፓልሴ፣ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።

May be an image of 7 people and indoor

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው ፤ ከጣሊያኑ ጀቨን ስካይ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ጋር ስምምነት በማድረግ ለቦይንግ-737 ማክስ አውሮፕላን የሚውል የኢንሱሌሽን ብላንኬት ማምረቻ ፋብሪካን እውን ማድረግ እንደተቻለ ገልጸዋል።

ፋብሪካውም የኢትዮጵያን የውጭ ምንዛሬንና የስራ እድል ፈጠራን በማሳደግ ጉልህ ጠቀሜታ እንዳለው ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር አጎስቲኖ ፓልሴ፥ የኢትዮጵያ አየር መንገድና የጣሊያኑ ስካይ ቴክኖ ግሮቭን ግሩፕ ስምምነት ወስደው ፋብሪካውን እውን ማድረጋቸው የጣሊያንና ኢትዮጵያን ትብብር የበለጠ ያሳድገዋል።

በቀጣይም ጣሊያን የኢትዮጵያን እድገትና ብልጽግና በመደገፍ የምታደርገውን በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ ትብብር አጠናክራ ትቀጥላለች ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም