አሸባሪው ህወሃት ከምስረታው ጀምሮ አላማው ከጠላቶች ጋር በማበር የኢትዮጵያን ህልውና በማዳከም መጨረሻም ማፍረስ ነው - ኢዜአ አማርኛ
አሸባሪው ህወሃት ከምስረታው ጀምሮ አላማው ከጠላቶች ጋር በማበር የኢትዮጵያን ህልውና በማዳከም መጨረሻም ማፍረስ ነው
መስከረም 11 ቀን 2015 (ኢዜአ) አሸባሪው ህወሃት ከምስረታው ጀምሮ አላማው ከጠላቶች ጋር በማበር የኢትዮጵያን ህልውና በማዳከም መጨረሻም ማፍረስ መሆኑን ኢዜአ ያነጋገራቸው አቶ ሙዑዝ ገብረ ህይወትና ጋዜጠኛ ፍሬዘር ነጋሽ ገለጹ።
አሸባሪው ህወሃት አጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብና በተለይም የትግራይ ክልል ህዝብ ጠላት በመሆኑ አገርን ከጥፋት ለመታደግ በጋራ መቆም ይገባል ብለዋል።
አሸባሪ ቡድኑ ከጥንትም የህዝቦችን በሰላም መኖር የማይሻ፤ ያለ ግጭት ህልውና የሌለው መሆኑን አስታውሰው አሁንም በዚሁ ተግባሩ ቀጥሎበታል ነው ያሉት።
የኢትዮጵያን ህልውና ለማጥፋት በማሰብ ባዘጋጀው ሰነድ ላይ በግልጽ የተቀመጠው ጽሁፍም ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከአሸባሪዎቹ አልሸባብና ከሸኔ ጋር እንደሚሰራ አመላክቷል፡፡
በስልጣን ዘመኑ ሞክሮ ያልተሳካለትን ኢትዮጵያን የመበታተን ዓላማው ዛሬ ለታሪካዊ ጠላቶች ፈረስ በመሆን ጭምር እኩይ ሃሳቡን ለማሳካት እየሰራ ይገኛል ነው ያሉት አቶ ሙኡዝ፡፡
አሸባሪው ቡድን ከውጭ ከአሸባሪው አል-ሸባብና ሌሎች የጥፋት ቡድኖች ጋር በመሆን ኢትዮጵያን ለማፍረስ አሁንም በጥረት ላይ ይገኛል ብለዋል።
በ1969 ዓ.ም ከሶማሌ ጦር ጋር በመሆን ኢትዮጵያን ወግቶ እንደነበር ያሥታወሱት አቶ ሙዑዝ፤ በቅርቡም ከአሸባሪው አልሸባብ ጋር በመተባበር ታሪካዊ ስህተቱን ደግሞታል ነው ያሉት።
በተለያዩ አካባቢዎች ሶስተኛ ዙር ጦርነት በመክፈት የመንግስትን የሰላም አማራጭ እንደማይቀበለው በግልጽ በማሳየት በጥፋቱ ቀጥሏል ብለዋል።
ጋዜጠኛ ፍሬዘር ነጋሽ በበኩሏ የህዝብ ሰብዓዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብት መከበር ጉዳይ የማያሳስበው አሸባሪው ህወሃት ለትግራይ ክልልም ሆነ ለመላው ኢትዮጵያ ዘላለማዊ ጠላት መሆኑን ገልፃለች።
የኢትዮጵያን ውደቀት ከሚመኙ ሃይሎችና አማጽያን ጋር በማበር ኢትዮጵያን ለማፍርስ መሻትም የቡድኑ መሰረታዊ ባህሪ መሆኑን ትናግራለች።
አሸባሪው ህወሃት በትግራይ ክልል ህዝብ ስም ሲነግድ ኖሮ አሁንም በተመሳሳይ ተግባሩ ቀጥሎ ብዙ መከራና ስቃይ እያስከተለ መሆኑን ተናግረዋል።
በተለይም የትግራይ ክልል ህዝብ አሸባሪ ቡድኑ ወደ ሰላማዊ ውይይት እንዲመጣ ጫና መፍጠር ከዚህ ካለፈም የህግ ተጠያቂ ማድረግና በእንቢተኝነቱ ከቀጠለም ሊዋጉት ይገባል ነው ያሉት።
የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች አሸባሪዎቹን ህወሃትና ሸኔ እንዲሁም ሌሎች የጥፋት ቡድኖችን በማስተባበር ሀገር ለማፍረስ እየሰሩ በመሆኑ ለኢትዮጵያ ህልውና ስንል ሁላችንም በጋራ መቆም ይጠበቅብናል ብለዋል።