ቀጥታ፡

የደቡብ ክልል ለአገር መከላከያ ሰራዊት የ 50 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

መስከረም 10 ቀን 2015 (ኢዜአ)የደቡብ ብሔር፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የሚውል የ50 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፉን በክልሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ እና የፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ባዮሽ ተስፋዬ እና የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ ተፈሪ አባተ ለገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ አስረክበዋል።

በዚሁ ወቅት ሚኒስትሩ እንዳሉት ሁሉም ክልሎች እና የኢትዮጵያ ህዝብ ለአገር መከላከያ ሰራዊት የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል።

አሸባሪው የሕወሃት ቡድን የከፈተብንን ጥቃት ለመመከት ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ እንደተለመደው ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

ድጋፉን ያስረከቡት ኃላፊዎች በበኩላቸው የክልሉ ህዝብና መንግስት ለሰራዊቱ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም