ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዳዲስ አውሮፕላኖችን በመግዛት የበረራ መዳረሻውን እያሳደገ ነው - የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው

መስከረም 10 ቀን 2015(ኢዜአ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዳዲስ አውሮፕላኖችን በመግዛት የበረራ መዳረሻውን እያሳደገ መሆኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ተናገሩ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ 129ኛ ዓለም አቀፍ መዳረሻውን ወደ ዮርዳኖስ መዲና አማን በማድረግ አዲስ የበራራ አገልግሎት ጀምሯል።

የአማን በረራ ወደ መካከለኛው ምስራቅ በሚደርገው በረራ 13ኛ መዳረሻ ሲሆን በሳምንት ሶስት ጊዜ በረራ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ጠሰው፤ በበረራ ማስጀመሪያ መርሐግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር ወደ ጆርዳኗ አማን ከተማ የሚደረገው በረራ የሁለቱን አገራት ሕዝቦች ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ትስስር ያጠናክረል ብለዋል።

አየር መንገዱ በዓመቱ በሰራቸው አመርቂ ተግባራት በአፍሪካና በዓለም አቀፍ ደረጃ ጭምር ምርጥ የጭነት አገልግሎት ክብር ማግኘቱን ጠቅሰዋል።

የበረራ መዳረሻዎቹን ለማሳደግም አዳዲስ አውሮፕላኖችን በመግዛት ወደ ስራ መግባቱን ዋና ስራ አስፈፃሚው ገልጸዋል።

አየር መንገዱ እስከ መጪው ታህሳስ መጨረሻ ድረስ አምስት ተጨማሪ አውሮፕላኖችን ከአምራቾች የሚረከብ መሆኑንም ተናግረዋል።

በባንግላዴሽ የኢትዮጵያ አምባሳደር ናዝሩል ኢስላም አየር መንገዱ ወደ አማን በሳምንት ሶስት ጊዜ የበረራ አገልግሎት መጀመሩን አስደሳች ዜና ብለውታል።

የበረራ አገልግሎቱ መጀመር ጆርዳናዊያን ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች የምስራቅ አፍሪካ አገራት መዳረሻቸው ለማድረግ ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዓለም አቀፍ መዳረሻውን ወደ 129 ያሳደገ ሲሆን ጥቅምት 20 ቀን 2015 ዓ.ም ደግሞ ወደ ስዊዘርላንዷ መዲና ዙሪክ በረራ ለመጀመር ዝግጅት ማድረጉ ታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም