የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሰፋ ከአለም ባንክ ተወካዮች ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሰፋ ከአለም ባንክ ተወካዮች ጋር ተወያዩ
መስከረም 10 /2014 (ኢዜአ) የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሰፋ ከአለም ባንክ ተወካዮች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙርያ ተወያዩ።
በውይይታቸው በኢትዮጵያ እየተተገበረ ባለው የአካባቢ ጥበቃ፣ የአየር ንብረት ለውጥ መቋቋምና መከላከል ላይ እየተሰራ ያለውን ስራ አንስተዋል።
ከብሔራዊ አካውንት መረጃ አያያዝና የተፈጥሮ ሃብትን በሀገራዊ ምርት እድገት ላይ ያለውን ድርሻ በተመለከተ ሚኒሰትሯ ከልዑካኑ ጋር መክረዋል።
በመረጃ አያያዝና መረጃን በአግባቡ መጠቀም በተመለከተ ሰፊ ውይይት መደረጉን የፕላንና ልማት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
የአለም ባንክ የሚደርገውን ድጋፍ የኢትዮጵያ መንግስት በ 10 ዓመቱ የልማት እቅድ ውስጥ ቅድሚያ ትኩረት በሰጣቸው መስኮች ላይ ማተኮር እንዳለበት የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሰፋ ተናግረዋል፡፡
የአለም ባንክ በተለያዩ መስኮች ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የጀመራቸውን የትብብርና የድጋፍ ስራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥልና ሀገሪቱ በጀመረቻቸውና ቅድሚያ በምትሰጣቸው መስኮች ላይ ድጋፉን እንደሚያጠናክር አስታውቋል፡፡