ቀጥታ፡

አሸባሪው ህወሃት በአማራና በአፋር ክልሎች 3 ሺህ 598 ንጹሃኖችን መግደልን ጨምሮ የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን መፈጸሙ ተጠቆመ

መስከረም 10 ቀን 2015 (ኢዜአ) አሸባሪው ህወሃት በአማራና በአፋር ክልሎች ከህግ ውጪ 3 ሺህ 598 ንጹሃን ሰዎችን መግደልን ጨምሮ በጦር ወንጀል የሚያስጠይቁ የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን መፈጸሙ ተጠቆመ።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን እና የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ፅህፈት ቤት የጋራ ምርመራ ዉጤቶችን ተከትሎ በኢትዮጵያ መንግስት የተቋቋመው የሚኒስትሮች ግብረ ሃይል የምርመራና ክስ ኮሚቴ የተፈጸመውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሲያጣራ መቆየቱ ይታወቃል።

May be an image of text that says "Areas North Shewa North Wollo Oromo National one 747 162 Summary of Extrajudicial Killings in Amhara and Afar regions Total otalNumber ofExtra-judicial Killings Perpetrator 257 TPLF and OLA TPLF TPLF and OLA TPLF TPLF TPLF TPLF TPLF TPLF TPLF TPLF TPLF Kombolcha Area and ts Environs Desse and its Environs ama, Wara Elu and Its Environs Woldiya and its Environs Lalibela and its Environs Sekota ndt Environs Waghmira Zone North Gonder Zone Debat, Debark woreda) Afar Region Total 108 515 124 1181 45 42 57 97 263 3598"

የግብረ ሃይሉ የምርመራና ክስ ኮሚቴ በአፋርና አማራ ክልሎች በሚገኙ ዘጠኝ አካባቢዎች የተፈጸሙ ጥፋቶችን የምርመራ ውጤት የመጀመሪያ ምዕራፍ ሪፖርቱን ረቂቅ አውጥቷል።

በዚህም በወልዲያ፣ ላሊበላ፣ ሰቆጣ፣ ጃማ ወረኢሉ፣ ደሴና ኮምቦልቻ አካባቢዎች እንዲሁም፣ ሰሜን ሸዋ ዞን፣ ኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን እና በአፋር ክልል እ.አ.አ ከመስከረም 15/2021 እስከ ጥር 31/2022 ድረስ የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን አጣርቷል።

የምርመራና ክስ ኮሚቴው ባደረገው ማጣራት ዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ ህግ የጣሱ በጦር ወንጀል የሚያስጠይቁ በርካታ ጥፋቶችን አሸባሪዎቹ ህወሃትና ሸኔ መፈጸማቸውን ማረጋገጡን ገልጿል።

በዚህም ከህግ ውጪ 3 ሺህ 598 ሰዎች ተገለዋል፣ 1 ሺህ 315 ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፣ 2 ሺህ 212 ሰዎች የአስገድዶ መድፈርና ጾታዊ ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል እንዲሁም 452 ሰዎች ሰብዓዊ ክብራቸው ተነክቷል ሲል ሪፖርቱ አመላክቷል።

ይህ አሰቃቂ የሆነ የሰብዓዊ መብት ጥሰት በአሸባሪዎቹ ህወሃት እና ሸኔ አማካኝነት መፈጸማቸውን ገልጿል።

ከህግ ውጪ የተፈጸመውን ግድያ በተመለከተ ሪፖርቱ እንዳመለከተው በወልዲያና አካባቢው ብቻ 1 ሺህ 181 ሰዎች በአሸባሪው ህወሃት ግድያ የተፈጸመባቸው መሆኑን ገልጿል።

በሰሜን ሸዋ እና በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞኖች አሸባሪዎቹ ህወሃትና ሸኔ በፈጸሙት ግድያ በሰሜን ሸዋ ዞን 257 ሰዎች እንዲሁም በኦሮሞ ብሔረሰብ 162 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል።

በአፋር ክልል ከፍተኛ ጥፋት ያደረሰው አሸባሪው ህወሃት የ263 ሰዎችን ህይወት መቅጠፉንም ሪፖርቱ ጠቁሟል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ፤

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም