የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለአፋር ክልል 14 ሚሊዩን ብር የሚገመት የአይነት ድጋፍ አደረገ - ኢዜአ አማርኛ
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለአፋር ክልል 14 ሚሊዩን ብር የሚገመት የአይነት ድጋፍ አደረገ
መስከረም 8 ቀን 2015 (ኢዜአ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለአፋር ክልል 14 ሚሊዩን ብር የሚገመት የአይነት ድጋፍ አድርጓል።
ድጋፉን ሰመራ ተገኝተው ለክልሉ ርእሰ መስተዳድር አወል አርባ ያስረከቡት የህዝብ ተወካዩች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ሎሚ በዶ ናቸው።
ድጋፉ 14 ሚሊዩን ብር የሚገመት የተለያዩ አልባሳት፣ፓስታ፣ ዘይትና በቆሎን ያካተተ ነው።
ምክትል አፈ ጉባዔዋ ሠመራ ሱልጣን አሊሚራህ አየር ማረፊያም ሲደርሱ መስተዳድር አቶ አወል አርባን ጨምሮ ከፍተኛ የክልሉ የስራ ሃላፊዎችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ምክትል አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ሎሚ በዶ እንዳሉት ድጋፉ የተወካዮች ምክር ቤት ሴት ተመራጮች ኮከስ በክልሉ በጦርነት ለተፈናቀሉ ወገኖች ያሰባሰቡት የሰብአዊ መሆኑን ገልጸዋል።