የሀድያ ብሄር የዘመን መለወጫ “ያሆዴ” በዓልን ምክንያት በማድረግ በሆሳዕና ከተማ አውደ ርዕይ ተከፈተ - ኢዜአ አማርኛ
የሀድያ ብሄር የዘመን መለወጫ “ያሆዴ” በዓልን ምክንያት በማድረግ በሆሳዕና ከተማ አውደ ርዕይ ተከፈተ
ሆሳዕና መስከረም 7/2014ዓ.ም |ኢዜአ|... የሀድያ ብሄር ዘመን መለወጫ “ያሆዴ” በዓልን ምክንያት በማድረግ የባህል ፌስቲቫል፣ የንግድ ኤግዚቢሽንና አውደ ርዕይ በሆሳዕና ከተማ ማምሻውን ተከፈተ።
የሀድያ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ አብርሃም ሌሊሾ እንዳሉት የኤግዚቢሽኑ ዋና ዓላማ የብሄሩን ባህላዊ እሴቶች ለማስተዋወቅና የተለያዩ ምርቶችን ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ ነው።
በዓውደ ርዕዩ የብሄሩ ባህላዊ እሴቶች እንደሚተዋወቁበት ገልጸዋል።
በበዓል ወቅት የሚስተዋለውን የዋጋ ንረት በመቆጣጠር ህብረተሰቡ የሚፈልገውን ግብዓት በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኝ ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥርም ጠቁመዋል።
የባህል ፌስቲቫል፣ ኤግዚቢሽኑና አውደ ርዕዩ እስከ መስከረም 16 ቀን 2015 ድረስ እንደሚቆይም ከወጣው መርሃ ግብር ማወቅ ተችሏል።