ቀጥታ፡

የኢትዮጵያን ዳር ድንበርና የህዝቦቿን ክብር እየጠበቀ ላለው የመከላከያ ሰራዊት ደም መለገስ ትንሹ ግዴታችን ነው

መስከረም 6/2015 (ኢዜአ) የኢትዮጵያን ዳር ድንበርና የህዝቦቿን ክብር እየጠበቀ ላለው የመከላከያ ሰራዊት ደም መለገስ ትንሹ ግዴታችን ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት አመራሮችና ሰራተኞች ገለጹ፡፡

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የሥራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ለጀግናዊ የሀገር መከላከያ ሰራዊት የደም ልገሳ መርሃ ግብር አካሂደዋል፡፡

የኢንተርፕራይዝ ልማቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ብሩ ወልዴ እንዳሉት የሀገር መከላከያ ሰራዊት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት በማስጠበቅ የመጨረሻው ምሽግ ነው፡፡

የኢትዮጵያን ዳር ድንበርና የዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ ቀን ከለሊት ለሚተጋው ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ደም መለገስ የዜጎች ትንሹ ግዴታ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የሥራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ለሰራዊቱ ደም በመለገስ ደጀንነታቸውን በተግባር እያሳዩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የሥራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ከዚህ ቀደም የተለያየ ድጋፈ ሲያደርጉ እንደነበር ገልጸው በቀጣይ ሌሎች ድጋፎችን እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም