ስንዴን ለውጪ ሀገር ገበያ ለማቅረብ ወደያዝነው ግብ ቀርበናል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ - ኢዜአ አማርኛ
ስንዴን ለውጪ ሀገር ገበያ ለማቅረብ ወደያዝነው ግብ ቀርበናል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ
መስከረም 6/2015 (ኢዜአ) በጀመርነው የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ስንዴን ለውጪ ሀገር ገበያ ለማቅረብ ወደያዝነው ግብ ቀርበናል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ዛሬ ጠዋት በኦሮሚያ ክልል የዱግዳ እና የቦራ ወረዳዎች የስንዴ ኩታ ገጠም እርሻ መመልከታቸውን ጠቅሰው ክንውን እጅግ ተስፋ የሰጪ መሆኑን ነው የገለጹት።
ግብርናን ማዘመን የላቀ ውጤት እንደሚያስገኝ የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የምሥራቅ ሸዋ ዞን ብቻውን 7 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ ማቀዱን አመላክተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ወረዳዎች የስንዴ ኩታ ገጠም እርሻን ጎብኝተዋል፡፡