በፈረንሳይ ፓሪስ ለተፈናቀሉ ወገኖች እና ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐግብር ይካሄዳል - ኢዜአ አማርኛ
በፈረንሳይ ፓሪስ ለተፈናቀሉ ወገኖች እና ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐግብር ይካሄዳል
መስከረም 05 ቀን 2015 (ኢዜአ) አሸባሪው ህወሃት በለኮሰው በጦርነቱ ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች እና ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐግብር ቅዳሜ መስከረም 07 ቀን 2015 ዓ.ም በፈረንሳይ ፓሪስ ይካሄዳል።
መርሐግብሩ የአዲስ ዓመት መግባትን በማስመልከት በሚዘጋጀው የባህል ፌስቲቫል ላይ እንደሚከናወን ኢዜአ ፓሪስ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ዳያስፖራው ማህበረሰብ በአንድነት እጅ ለእጅ በመያያዝ ለግድቡ ግንባታና በጦርነት ለተጎዱ ወገኖች የገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርጉ በኤምባሲው ጥሪ ቀርቧል።
የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐግብሩን በፈረንሳይ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አባላት ከኢትዮ-ፈረንሳይ ወዳጅነት ማህበር፣ በፈረንሳይ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የድጋፍ ማስተባባሪያ ምክር ቤትና ሌሎች አጋሮች በትብብር ያዘጋጁት እንደሆነ ተገልጿል።