ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ደም በመለገስ ህዝባዊ ደጀንነትን በተግባር ማሳየት ይገባል-- ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ

163

መስከረም 3/2015 (ኢዜአ) የኢትዮጵያን የግዛት አንድነትና የህዝቡን ደህንነት ለማስከበር በግንባር ለሚዋደቀው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ደም በመለገስ ህዝባዊ ደጀንነትን በተግባር ማሳየት እንደሚገባ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ ገለጹ፡፡

የሚኒስቴር መስሪያቤቱ የሥራ ኃላፊዎችና  ሠራተኞች  ለሀገር  መከላከያ  ሰራዊት  ደም  ለግሰዋል፡፡

ሚኒስትሯ ወይዘሮ  ጫልቱ ሳኒ  እንዳሉት አሸባሪው  የህወሓት  ቡድን  የመንግስትን  የሰላም ጥሪ ወደ ጎን በመተው ለሶስተኛ ጊዜ ወረራ በመፈጸም በንጹሃን ዜጎችና ንብረት  ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው፡፡

የሽብር ቡድኑን ድርጊቱ ለማስቆም ሰራዊቱ  ህዝቡን  ደጀን  አድርጎ  እየተከላከለ መሆኑንም እንዲሁ፡፡

በመሆኑም የሀገር መከላከያ ሰራዊትን አቅም ለማጠናከር ህዝቡ በሚችለው ሁሉ ለመደገፍየሚያደርገው እንቅስቃሴ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

የኢትዮጵያን የግዛት አንድነትና የህዝቡን ደህንነት ለመጠበቅ በከፍተኛ ጽናት ላይ የሚገኘውን የሀገር መከላከያ ሰራዊት ደም በመለገስም ሆነ በሌላ አቅም በፈቀደው ደጀን መሆን እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎችና ሰራተኞችም "ኢትዮጵያን የማዳን ጥሪ የተላለፈለት ሁሉ በሚችለው መደገፍ አለበት" በሚል መርህ  ደም መለገሳቸውን  ገልጸዋል፡፡

የሽብር ቡድኑ የትግራይን  ሕዝብ  እንደማይወክል  ገልጸው፤  የችግሩ  ገፈት  ቀማሽ  የሆነው የትግራይ ህዝብም ቆም ብሎ ማሰብ አለበት ብለዋል፡፡

የትግራይ እናቶች ለጥቂት የሽብር ቡድኑ አባላት ጥቅም ሲባል የልጆቻቸው ህይወት እየተቀጠፈ በመሆኑ የሽብር ቡድኑን የጦርነት ጉዞ በቃ ሊሉ እንደሚገባ አንስተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም