በ133 ሚሊዮን ብር ካፒታል የተቋቋመው የጀብዱ ሞተርስ አክስዮን ማኅበር ፋብሪካ ተመረቀ - ኢዜአ አማርኛ
በ133 ሚሊዮን ብር ካፒታል የተቋቋመው የጀብዱ ሞተርስ አክስዮን ማኅበር ፋብሪካ ተመረቀ

መስከረም 03 ቀን 2015(ኢዜአ) በኦሮሚያ ክልል ቢሾፍቱ ከተማ በ133 ሚሊዮን ብር ካፒታል የተቋቋመው የጀብዱ ሞተርስ አክስዮን ማኅበር ፋብሪካ ተመረቀ።
በምረቃ ስነ ስርአቱ ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሽመልስ አብዲሳ፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ።
ከፋብሪካው ምርቃት መርሐግብር በተጨማሪ ለአርሶ አደሮች በፋብሪካው የተገጣጠሙ ከ16ሺህ በላይ የውሀ መሳቢያ ፓምፖች ርክክብ የሚደረግ ይሆናል ።

የፋብሪካው ስራ መጀመር የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ፣ ለስራ እድል ፈጠራና ከውጭ የሚገቡ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በሀገር ውስጥ ለመተካት እንደሚያግዝ ተጠቁሟል።
ለተጠቃሚዎች የሚተላለፉት የውሀ ፓምፖችም 75 ሺህ ሄክታር መሬት ለማልማት የሚያግዙ መሆናቸው ተጠቅሷል።