በድብቅ የሚሰሩ ኃይሎች በኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ሕልውና ላይ ጥቃት ከፍተዋል-አምባሳደር ስለሺ በቀለ - ኢዜአ አማርኛ
በድብቅ የሚሰሩ ኃይሎች በኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ሕልውና ላይ ጥቃት ከፍተዋል-አምባሳደር ስለሺ በቀለ
መስከረም 3 ቀን 2015 (ኢዜአ) “በድብቅ የሚሰሩ ኃይሎች በኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ሕልውና ላይ ጥቃት ከፍተዋል” ሲሉ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስለሺ በቀለ ገለጹ።
አምባሳደሩ አሸባሪው ሕወሓት የኢትዮጵያን ልማት ከማይፈልጉ የረጅም ጊዜ ጠላቶቿ የጦር መሳሪያ ድጋፍ እያገኘ ነው ብለዋል።
“በአሸባሪው ሕወሓት አማካኝነት የተጀመረው ጦርነት አንድ ቡድን ብቻ የጋረጠው ፈተና ብቻ ተደርጎ መታየት የለበትም ይልቁንም በድብቅ የሚሰሩ አካላት በኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ሕልውና ላይ የከፈቱት ጥቃት ነው” ሲሉ አምባሳደር ስለሺ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።
የኢትዮጵያን ልማት የማይፈልጉ የረጅም ጊዜ ጠላቶች የሽብር ቡድኑን በጦር መሳሪያ እየደገፉ መሆኑን አመልክተዋል።
ኢትዮጵያውያን የተቃጣባቸውን ጥቃት በጋራ መከላከል ይገባቸዋል ነው ያሉት አምባሳደሩ በመልዕክታቸው።