ቀጥታ፡

እኛ ኢትዮጵያውያን የአንድነትን ሀያልነት እና አሸናፊነት በታሪክ ጠንቅቀን እናውቃለን - ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ

ጳጉሜን 05 ቀን 2014 (ኢዜአ) እኛ ኢትዮጵያውያን የአንድነትን ሀያልነት እና አሸናፊነት በታሪክ ጠንቅቀን እናውቃለን ሲሉ የሀረሪ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ተናገሩ፡፡

የአንድነት ቀንን ስናከብር "በአንድነት ከመከላከያ ሰራዊቱ ጎን በመቆም" ሊሆን ይገባልም ብለዋል፡፡

የአንድነት ቀን በሀረሪ ክልል "ስናብር ስናምር" በሚል መሪ ቃል በዛሬው እለት በመከበር ላይ ይገኛል።

እኛ ኢትዮጵያውያን የአንድነትን ሀያልነት እና አሸናፊነት የአድዋ ድል፣ የአክሱም ሀውልት፣ የጀጎል ግንብ እና ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በአንድነት ከተመዘገቡት ድሎች መካከል ተጠቃሽ መሆናቸውን ተናግረዋል።

May be an image of 4 people and people standing

በኢትዮጵያ የታሪክ ማህደር አገር አደጋ ላይ ስትወድቅ ዝም የሚል ዜጋ አልነበረም አሁንም ቢሆን በአገር ጉዳይ የሚደራደር ዜጋ የለም ሲሉም ተናግረዋል::

አሸባሪው የህወሃት ቡድን የሰላም አማራጩን በመግፋት አገሪቱ ላይ የከፈተውን ወረራ ለመመከት የመከላከያ ሰራዊቱ ብርቱ ክንዶችን እያሳረፈበት ይገኛል ያሉ ሲሆን ሁሉም ዜጋ ከመከላከያ ሰራዊቱ ጎን በመቆም የሚጠበቅበትን ሚና ሊወጣ ይገባል ብለዋል።

የክልሉ መንግስት የአገር ሉአላዊነትን ለማስከበር እየተዋደቀ ለሚገኘው ሰራዊት የሚያደረገው ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

የሀረሪ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሃላፊ ሄኖክ ሙሉነህ ቀኑ ኢትዮጵያ አንድነቷን ጠብቃ የኖረች አገር መሆኗን እና ልዩነቶቻችንን እንደ ችግር ሊጠቀሙበት ለሚፈልጉ ሀይሎች አንድነታችንን የምናሳይበት ነው ብለዋል።

አቶ ሄኖክ ችግሮችን በመሻገር አገር ሉአላዊነቷ ተጠብቆ የምትቀጥለው አንድ ሆነን ስንቆም በመሆኑ አንድነትን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎችም ጠላት በለኮሰው እሳት እራሱ እንደሚቃጠል እና በጀግናው የመከላከያ ሰራዊት ድል እንደሚደረግ እምነታቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ጠላቶች ተላላኪ የሆነው አሸባሪው ህወሃት በተባበረ ክንድ ይደመሰሳል ብለዋል።

የአገር ሉአላዊነትን ለማስጠበቅ አንድነታቸውን አጠናክረው አንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

በመርሀ ግብሩ ላይ የተለያዩ አካላት የተገኙ ሲሆን ህብረተሰቡን ያለ ልዩነት በማገልገል ኢትዮጵያን ከፍ ለማድረግ ቃለ-መሀላ ፈፅመዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ፤

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም