አምባሳደር ሲለሺ በቀለ ዳያስፖራዎች በአዲሱ ዓመት የአገራቸውን ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እንዲያጠናክሩ ጠየቁ - ኢዜአ አማርኛ
አምባሳደር ሲለሺ በቀለ ዳያስፖራዎች በአዲሱ ዓመት የአገራቸውን ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እንዲያጠናክሩ ጠየቁ
ጳጉሜ 5 ቀን 2014 (ኢዜአ) አምባሳደር ሲለሺ በቀለ በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዳያስፖራዎች በአዲሱ ዓመት ለአገራቸው የሚያደርጉትን ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እንዲያጠናክሩ ጠየቁ ።
በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ስለሺ በቀለ በመላው አሜሪካ ለሚገኙ ኢትጵያውያን የ2015 ዓ.ም አዲስ ዓመትን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
አምባሳደሩ በመልካም ምኞት መልዕክታቸውም በመላው አሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወገኖች አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የፍቅር እና የአንድነት እንዲሆን ልባዊ ምኞታቸውን ገለጸዋል ።
አክለውም ለአገራችሁ እያደረጋችሁ ያላችሁትን ሁሉን አቀፍ ድጋፍ አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ ከአደራ ጭምር እጠይቃለሁ ብለዋል፡፡