ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ መንግስት አለምአቀፉ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ያወጣው መግለጫ እንዳሳዘነው ገለጸ

ጳጉሜን 04 ቀን 2014 (ኢዜአ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አለምአቀፉ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ኢትዮጵያን አስመልክቶ ከትናንት በስቲያ ያወጣው መግለጫ የሚያሳዝን መሆኑን ገለጸ።

ኮሚሽኑ የሰብአዊ መብት ጉዳዮችን ለፖለቲካዊ አላማው ማስፈጸሚያነት ማዋሉንም አመልክቷል።

ሚኒስቴሩ ዛሬ በማህበራዊ ትስስር ገጹ፤ ኮሚሽኑ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ተገቢውን እውቅና ለመስጠት ምንም አይነት ብቃት የለውም ብሏል።

ኮሚሽኑ የጸጥታው ምክር ቤት ኢትዮጵያ ላይ እርምጃ እንዲወስድ ያቀረበው ግልጽ ያልሆነ ጥሪ የኮሚሽኑን ግድ የለሽ ባህሪ የሚያሳይ ከመሆኑም ባሻገር ኢትዮጵያ ላይ ፖለቲካዊ ፍላጎት እንዳለው ማሳያ ነው ብሏል።

ኮሚሽኑ የሰብአዊ መብት ጉዳዮችን ፖለቲካዊ ጫና ለማሳደር እንደ መሳሪያነት እየተጠቀመበት መሆኑ እውነተኛ ማንነቱን ያሳየበት እና ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ያለውን የትብብር በር ሙሉ ለሙሉ የዘጋበት ነው ብሏል።

መንግስት የሰብአዊ መብቶች በኢትዮጵያ እንዲከበሩ እና አጥፊዎችን ለህግ ለማቅረብ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመረጃው አስታውቋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ፤

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም