ኢዜአ አዲስ አመትን ምክንያት በማድረግ ለተማሪዎች የገንዘብና የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ - ኢዜአ አማርኛ
ኢዜአ አዲስ አመትን ምክንያት በማድረግ ለተማሪዎች የገንዘብና የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ
ጳጉሜን 2/2014 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት /ኢዜአ/ አዲስ አመትን ምክንያት በማድረግ ለተማሪዎች የገንዘብና የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።
በኢዜአ የሴቶችና ባለብዙ ዘርፍ ዳይሬክተር ታደለች ቦጋለ፤ የተቋሙ ሰራተኞች በሚያደርጉት መዋጮ በቋሚነት ድጋፍ የሚያደርግላቸው ተማሪዎች መኖራቸውን ጠቅሰዋል።
በዛሬው እለትም አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ለተማሪዎቹ የገንዘብና የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ አጋርነቱን አሳይቷል ብለዋል።
በድጋፉ ለእያንዳንዱ ተማሪዎች የ2 ሺህ ብር ስጦታና የትምህርት ቁሳቁስ አንዲሁም የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ የትምህርት መርጃ መሳሪያ (አጋዥ መጽሀፍት) ተበርክቶላቸዋል ብለዋል።
ኢዜአ በመረጃ ተደራሽነት አስተማማኝ የዜና ምንጭ ከመሆን ባለፈ በማህበራዊ ሃላፊነትም የተለያዩ ተሳትፎዎችን በማድረግ ላይ መሆኑን ጠቅሰው ይሄው ተግባሩ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንም አረጋግጠዋል።