ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ ለውጭ ባለሃብቶች ክፍት እንዲሆን መወሰኑ ለምጣኔ ሃብት እድገት ቁልፍ ርምጃ ነው- የምጣኔ ሀብት ምሁር

ጳጉሜን 1/2014(ኢዜአ) የኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ ለውጭ ባለሃብቶች ክፍት እንዲሆን መወሰኑ ለምጣኔ ሃብት እድገት ቁልፍ ርምጃ መሆኑን የምጣኔ ሃብት ተመራማሪ ገለጹ።

 የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከጥቂት ቀናት በፊት ባካሄደው 13ኛ መደበኛ ስብሰባ የባንክ ዘርፉን ለውጭ ኢንቨስተሮች ክፍት ለማድረግ በቀረበ ፖሊሲ ላይ ተወያይቶ በሥራ ላይ እንዲውል መወሰኑ ይታወቃል። 

በዚሁ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት በኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ባለሙያዎች ማህበር ተመራማሪ አደም ፊቶ፤ የባንክ ዘርፉ ለውጭ ባለሃብቶች ክፍት መደረጉ ምጣኔ ሃብቱን ለማሳደግ እየተወሰዱ ካሉ እርምጃዎች መካከል የሚጠቀስ ነው ብለዋል።

በቀጣይ የውጭ ሀገር ባንኮች በኢትዮጵያ ሲሰማሩ የሀገሪቱን የፋይናንስ ዘርፍ አቅም በማሻሻል በኩል አስተዋጽኦ እንደሚኖረውም ነው የገለጹት።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በ2014 ዓ.ም በፓርላማ ባደረጉት ንግግር የባንክ ዘርፉ ለበርካታ ዓመታት ለውጭ አገር ባንኮች ዝግ ሆኖ መቆየቱ የሀገር ውስጥ ባንኮችን ተጠቃሚ አድርጎ መቆየቱን ማንሳታቸው ይታወሳል።"ከአሁን በኋላ ባንኮች በዘመናዊ አሰራርናና በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እራሳቸውን ማዘጋጀት አለባቸው" ሲሉ ጠቁመው ነበር። 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም