ቀጥታ፡

አሸባሪው ሕወሓት ዳግም የከፈተውን ጦርነት የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ በዋሺንግተን ዲሲ እየተካሄደ ነው

ጳጉሜን 01 ቀን 2014 (ኢዜአ) በአሜሪካ ዋሺንግተን ዲሲ አሸባሪው ሕወሓት ዳግም የከፈተውን ጦርነት የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።

ሰልፉ “በአገር ሕልውናና አንድነት አንደራደርም!” በሚል መሪ ሀሳብ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ፊት ለፊት እየተከናወነ ይገኛል።

ሰልፉ አሸባሪው ሕወሓት ዳግም የከፈተውን ጦርነት ለማውገዝና የአገርን ሕልውና ለማስጠበቅ እየተሳተፉ ላሉ ለአገር መከላከያ ሰራዊት፣ ለጸጥታ ኃይሎችና ዜጎች ድጋፍና አጋርነትን የመግለጽ አላማ እንዳለው የሰላምና አንድነት ለኢትዮጵያ ዲሲ ግብረ ኃይል ለኢዜአ ገልጿል።

May be an image of 7 people, people standing and outdoors

የአሜሪካ መንግስት የኢትዮጵያና ኤርትራ ላይ ያለውን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ በመከባበርና በሁለትዮሽ የጋራ ጥቅም ላይ ያተኮረ እንዲሆን የሚያሳስቡ መልዕክቶች በሰልፈኞቹ ተላልፈዋል።

በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ትውልደ-ኢትዮጵያውያንና ሌሎች የኢትዮጵያ ወዳጆች ተሳትፈዋል።

የሰላምና አንድነት ለኢትዮጵያ ግብረ ኃይል ሰልፉን ከአገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ጋር በትብብር እንዳዘጋጀውም ተገልጿል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ፤

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም