ቀጥታ፡

በዓረቡ አለም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አሸባሪው ሕወሓት የሚያሰራጨውን ሐሰተኛ መረጃ እንዲመክቱ ጥሪ ቀረበ

ጷጉሜን 1 2014(ኢዜአ) በዓረቡ አለም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የአሸባሪው ሕወሃት የዲጂታል ክንፍ የሚሰራጨውን ሐሰተኛ መረጃ በማጋለጥና በመመከት ኢትዮጵያን እንዲደግፉ ጥሪ ቀረበ።

በኳታር የኢትዮጵያ ኤምባሲ የኢትዮጵያን አዲስ ዓመት በተለያዩ መረኃ ግብሮች አክብሯል።

በመርሐግብሩ ላይ ከ200 በላይ በኳታር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ የተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማቶች እና አምባሳደሮች ተገኝተዋል።

May be an image of 3 people and indoor

በኳታር የኢትዮጵያ አምባሳደር ፈይሰል አሊዪ በዚህ ወቅት ባደረጉት ገለጻ በዓረቡ አለም የሚኖሩ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አባላት መንግስት ከአሸባሪው ሕወሃት የተቃጣበትን ጥቃት ለመመከት የሚያደርገውን ጥረት እንዲደግፉ ጥሪ አስተላልፈዋል።

በአሸባሪው ሕወሃት ዲጂታል ክንፍ እየተሰራጨ ያለውን የሐሰት መረጃ በመመከትና በማጋለጥም ድጋፋቸውን እንዲያጠናክሩ ጠይቀዋል።

እንደ ታላቁ የህዳሴ ግድብ የመሳሰሉት ታላላቅ ፕሮጀክቶች እስኪጠናቀቁ ድጋፋቸውን እንዲቀጥሉ ነው ጥሪ ያቀረቡት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም