አየር መንገዱ ወደ ብራዚልና አርጀንቲና ዕለታዊ በረራ ጀመረ - ኢዜአ አማርኛ
አየር መንገዱ ወደ ብራዚልና አርጀንቲና ዕለታዊ በረራ ጀመረ
ጷጉሜን 1 ቀን 2014(ኢዜአ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ብራዚል እና አርጀንቲና ዕለታዊ በረራ መጀመሩን አስታወቀ፡፡
ዕለታዊ በረራውን የጀመረው በብራዚል ሳኦፖሎ እና በአርጀንቲና ቦነስ አይረስ ከተሞች መሆኑን በደቡብ አሜሪካ የአየር መንገዱ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሚካኤል በቀለ ተናግረዋል፡፡
አየር መንገዱ ወደ ከተሞቹ ለሚያደርገው ዕለታዊ በረራ ቦይንግ 787-8 ድሪምላይነር ዘመናዊ አውሮፕላኖችን እንደሚጠቀምም ዳይሬክተሩን ጠቅሶ ኤር ዌይስ ማኔጂንግ ድረ-ገጽ አስነብቧል፡፡
ከቀናት በፊት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቶኪዮ ከተማ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተሳፋሪዎችን በማጓጓዝ ኢንቺዮን ኤርፖርት ከተሰኘ የአየር መንገዶች ጥምረት ዕውቅና እንደተቸረው ይታወሳል።