ቀጥታ፡

አሸባሪው ሕወሓት ዳግም የከፈተውን ጦርነት የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬ በዋሺንግተን ዲሲ ይካሄዳል

ጳጉሜን 01 ቀን 2014 (ኢዜአ) በአሜሪካ ዋሺንግተን ዲሲ አሸባሪው ሕወሓት ዳግም የከፈተውን ጦርነት የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬ ይካሄዳል።

ሰልፉ “በአገር ሕልውናና አንድነት አንደራደርም!” በሚል መሪ ሀሳብ ከቀኑ 10 ሰአት ጀምሮ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ፊት ለፊት እንደሚካሄድ ኢዜአ ከሰላምና አንድነት ለኢትዮጵያ ግብረ ኃይል ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ሰልፉ አሸባሪው ሕወሓት ዳግም የከፈተውን ጦርነት ለማውገዝና የአገርን ሕልውና ለማስጠበቅ እየተሳተፉ ላሉ ለአገር መከላለከያ ሰራዊት፣ ለጸጥታ ኃይሎችና ዜጎች ድጋፍና አጋርነትን የመግለጽ አላማ እንዳለው ገልጿል።

በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ሌሎች የኢትዮጵያ ወዳጆች ይሳተፉበታል ተብሎ ይጠበቃል።

በአሜሪካ የሚገኙ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አባላት በሰልፉ ላይ በመሳተፍ አጋርነታቸውን እንዲያሳዩ ጥሪ ቀርቧል።

የሰላምና አንድነት ለኢትዮጵያ ግብረ ኃይል ሰልፉን ከአገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ጋር በትብብር እንዳዘጋጀውም ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም