የኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም፣ ልማትና አንድነት በተጠናከረ መልኩ እንዲቀጥል ወጣቶች የላቀ ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል- የወጣቶች ፌደሬሽን - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም፣ ልማትና አንድነት በተጠናከረ መልኩ እንዲቀጥል ወጣቶች የላቀ ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል- የወጣቶች ፌደሬሽን
ነሃሴ 30 ቀን 2014(ኢዜአ) የኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም፣ ልማትና አንድነት በተጠናከረ መልኩ እንዲቀጥል ወጣቶች የላቀ ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ወጣቶች ፌደሬሽን ገለጸ።
የፌደሬሽኑ ምክትል ፕሬዝዳንት ጽጌሬዳ ዘውዱ፤ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም በአገራዊ ሁለንተናዊ ልማትና እድገት የወጣቶች ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።
በመሆኑም የኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም፣ ልማትና አንድነት በተጠናከረ መልኩ እንዲቀጥል ወጣቶች የላቀ ሚናቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።
አሸባሪው ህወሃት ኢትዮጵያን አፈርሳለሁ ብሎ የተለያዩ የጥፋት እቅዶችን ይዞ እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው እኩይ ዓላማውን ለማክሸፍ ሁላችንም መዘጋጀት አለብን ብለዋል።
"የአገር አለኝታና መከታ በመሆን በተለይም ወጣቶች አገራዊ ሃላፊነታችንን እንወጣ" በማለትም መልእክት አስተላልፈዋል።
ኢትዮጵያውያን በእውቀታቸው፣ በገንዘብና በሌሎችም አጋጣሚዎች ሁሉ ለአገራቸውና ለህዝባቸው የድርሻቸውን እንዲያበረክቱም ጠይቀዋል።
የኢትዮጵያ ወጣቶች ፌዴሬሽን የወጣቶችን ፓለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትና ተሳትፎ ለማሳደግ በማለም በ2001 ዓ.ም መመስረቱ ይታወቃል።