ሊዝ ትረስ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተመረጡ

746

ነሐሴ 30 ቀን 2014(ኢዜአ) ሊዝ ትረስ አዲሷ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር መሆናቸው ተገለጸ።

ትረስ ተፎካካሪያቸው የሆኑትን ሪሺ ሱናክን በማሸነፍ ነው የተመረጡት።

ሊዝ ትረስ 81 ሺህ 326 ድምጽ ያገኙ ሲሆን ሪሺ ሱናክ ደግሞ 60 ሺህ 339 ድምጽ ማግኘታቸው ነው የተገለጸው።

አዲሷ ጠቅላይ ሚኒስትር ወደ ፖለቲካው ዘርፍ ከመግባታቸው በፊት የሂሳብ አያያዝ እና የኢኮኖሚ ባለሙያ ሆነው ሰርተዋል።

ቀደም ሲል የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ምክትል የገንዘብ ሚኒስትር እና የግምጃ ቤት ሚኒስትር በመሆን በተለያዩ የመንግስት የኃላፊነት ቦታዎች ማገልገላቸውም ተመልክቷል።

ጠቅላይ ሚኒሰትሯ በብራታኒያ እየጨመረ የመጣውን የዋጋ ንረት፣ ከብሬግዚትና በዩክሬን እየተካሄደ ካለው ጦርነት ተያይዞ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ላይ እያጋጠሙ ያሉ ፈተናዎችን መፍታት እንደሚጠበቅባቸው ሮይተርስ በዘገባው አመላክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም