በክልሉ የተከናወኑ የጸጥታ ማስከበር እና የልማት ስራዎች የግምገማ መድረክ እየተካሄደ ነው

101

ነሐሴ 29 ቀን 2014 (ኢዜአ)በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በ2014 በጀት ዓመት የተከናወኑ የጸጥታ ማስከበር እና የልማት ስራዎች የግምገማ መድረክ ዛሬ በአሶሳ መካሄድ ጀመረ።

መድረኩ በክልሉ በመተከል ዞን እየተረጋጋ የመጣውን ሠላም በማጠናከር በካማሺ እና ማኦኮሞ ልዩ ወረዳ ዘላቂ ሰላም ማስፈንን ዓላማ ያደረገ መሆኑ ተገልጿል።

በግምገማ መድረኩ የመተከል፣ካማሺ እና አሶሳ ዞኖች እንዲሁም የአሶሳ ከተማ አስተዳደር የ2014 የጸጥታ ማስከበር እና የልማት ስራቸውን የሚመለከት ዝርዝር ሪፖረት እያቀረቡ ነው።

በቀጣይ የክልሉ የጸጥታ ግብረ ሃይል የተጠቃለለ ሪፖርት የሚቀርብ ሲሆን በመድረኩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሃሰንን ጨምሮ የክልልና የፌደራል ከፍተኛ አመራሮች እየተሳተፉ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም