ለህዝባችን ሰላምና ጥቅም ስንል ከመንግስትና ከመከላከያ ስራዊታችን ጎን እንቆማለን- የኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተግባር ምክር ቤት - ኢዜአ አማርኛ
ለህዝባችን ሰላምና ጥቅም ስንል ከመንግስትና ከመከላከያ ስራዊታችን ጎን እንቆማለን- የኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተግባር ምክር ቤት
ነሐሴ 28 ቀን 2014(ኢዜአ) ለህዝባችን ሰላምና ጥቅም ስንል ከመንግስትና ከመከላከያ ስራዊታችን ጎን በመቆም የዜግነት ድርሻችንን እንወጣለን ሲል የኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተግባር ምክር ቤት አስታወቀ።
ምክር ቤቱ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙርያ ጋዜጣዊ መግለጫ አውጥቷል።
በመግለጫው ሀገራችን ኢትዮጵያ ተገዳ የገባችበትን የሕልውና ጦርነት በጋራ ለመመከት በመላው አለም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከሕዝባቸው ጎን በቆራጥነት በመቆም የሐገርን አላዊነት ለማሰከበር በሚደረገው ዘመቻ የዜግነት ግዴታቸውን እንዲወጡ ጥሪያችንን እናቀርባለን ብሏል።
ይህ የህልውና ጦርት በውጭ ሀገር የምንገኘውን ኢትዮጵያውያን እንቅልፍ የነሳና ሐገራችን እንደ ሐገር እንዳትቀጥል በወያኔ ጁንታ ቡድን፣ በአልሻባብና በሸኔ እንዲሁም በውጭ ሐገር የሚገኙ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች በቅንጅት የከፈተብን ጦርነት ብሔራዊ ክብራችንን የሚነካና የሀገራችንን ሰላም የሚያውክ በመሆኑ በእጅጉ አሳስቦናል ነው ያለው።
ስለዚህ መንግስት በሆደሰፊነት ቀደም ሲል የወሰዳቸውን ቁርጠኛ የሰላም ፍላጎቶቹ በማድነቅ የሰላም አማራጩ ውጤታማ እንዲሆን ሙሉ ድጋፍ ስንሰጥ መቆየታችን ይታወቃል ብሏል።
በአሸባሪነት የተፈረጃት ፀረ ሰላም ሐይሎች ከሰላም ይልቅ ጦርነትንና አልቂትን መርጠው የከፈቱብንን የአጥፍቶ መጥፋት ጦርነት በጥብቅ አውግዘን መንግስት እየወሰደ ያለውን አርምጃ እንደግፋለንም ሲል ምክር ቤቱ ገልጿል።
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተግባር ምክር ቤት የአሸባሪውን ጁንታ ቡድን እንዲሁም አልሻሸባብና ሸኔን በማውገዝ ብቻ ሳይሆን ለሐገር ሕልውናና ለህዝባችን ሰላምና ጥቅም ስንል ከመንግስት እንዲሁም ከመከላከያ ስራዊታች ጎን በመቆም የዜግነት ድርሻችንን ለመወጣት የተግባር ምክር ቤቱ ዝግጁ መሆናችንን እናረጋግጣለን ብሏል።
በሐገራችን ውስጥ በተፈጠረው ሐገር የማዳን ዘመቻ በዘር፣ በሃይማኖት በፖቲካ እምነት ሳንከፋፈል ከስሜታዊነትና ከኩሪፊያ በመውጣት ለነገ ኢትዮጵያ የተሻ ነገ ለማምጣት ትግሉ የሚጠይቀውን ማንቸውንም ድጋፍ እንድናደርግ ብሏል ምክር ቤቱ።
መንግስት ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ ከፍታ ለማድረስ የፖለቲካ ችግሮችን በአግባቡ ፈትሾ ሁሉን አቀፍ ውይይት ለማድረግ እያከናወነ የሚገኘውን ተግባር ምክር ቤቱ መደገፉን ይቀጥላል ሲል አመልክቷል።