ዩኒቨርሲቲዎቹ ከ6ሺህ 717 በላይ ተማሪዎችን እያስመረቁ ነው - ኢዜአ አማርኛ
ዩኒቨርሲቲዎቹ ከ6ሺህ 717 በላይ ተማሪዎችን እያስመረቁ ነው
ጎንደር እና ሰመራ (ኢዜአ) ነሀሴ 28/2014 ጎንደር እና ሰመራ ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን ከ6ሺህ 717 በላይ ተማሪዎችን ዛሬ እያስመረቁ ነው።
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ካስመረቃቸው 5ሺህ 527 ተማሪዎች መካከል 1ሺህ 600 ሴቶች ናቸው።
ተመራቂዎቹ በመጀመሪያ፣ በሁለተኛ እና በሦስተኛ ዲግሪ የትምህርት መስኮች የሰለጠኑ መሆናቸውም ተገልጿል።በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ሥራ አስፈጻሚ ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ተከተል ዮሐንስ በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን የተመራቂ ወላጆች ታድመዋል።
በተመሳሳይ ዜና የሰመራ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ1ሺህ 190 በላይ ተማሪዎችን እያስመረቀ ይገኛል።
ከተመራቂዎቹ መካከል ከ547ቱ በመደበኛ የትምህርት መርሃ-ግብር በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ የሰለጠኑ ናቸው።
ቀሪዎቹ ተመራቂዎች በክረምት እና በማታ የትምህርት መርሃ ግብሮች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ መሆናቸው በምረቃው ላይ ተገልጿል።
በመርሃ-ግብሩ ላይ የዩኒቨርሲቲው የቦርድ ሰብሳቢና አመራሮችን ጨምሮ የአፋር ክልል ከፍተኛ አመራሮች መገኘታቸው ታውቋል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።