ቀጥታ፡

ለተፈናቀሉ ዜጎች የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐግብር በዋሺንግተን ዲሲ እንደሚካሄድ ተገለጸ

ነሐሴ 26 2014(ኢዜአ) ለተፈናቀሉ ዜጎች የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐግብር የፊታችን ቅዳሜ በዋሺንግተን ዲሲ ይካሄዳል።

መርሐግብሩ “ወገን ለወገን” በሚል መሪ ሀሳብ በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከናወናል።

ከዝግጅቱ የሚሰበሰበው ገንዘብ ለተፈናቀሉ ዜጎችና በተለያዩ ምክንያቶች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ ወገኖች ማቋቋሚያ እንደሚውል ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተግባር ቡድን ለኢዜአ በላከው መግለጫ አስታውቋል።

በመርሐግብሩ ላይ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስለሺ በቀለ፣ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ፣ጋዜጠኛ ሄርሜላ አረጋዊና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ከሁለት ሳምንት ገደማ በፊት በአሜሪካ ዋሸንግተን ዲሲ በአንድ ምሽት በተካሄደ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐግብር ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ የሚውል ከ70 ሺህ ዶላር በላይ መሰብሰቡ የሚታወስ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም