ቀጥታ፡

አሸባሪው ህወሓት የጀመረውን የጥፋት ጉዞ ለሰላም ዘብ በመቆም እንገታዋለን- በብልጽግና ፓርቲ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሴቶች ሊግ

ነሐሴ 24 ቀን 2014(ኢዜአ) አሸባሪው ህወሓት ለሠላም የተዘረጋውን የኢትዮጵያን እጅ ነክሶ የጀመረውን የጥፋት ጉዞ ለሠላማችን ዘብ በመቆም እንገታዋለን ሲሉ በብልጽግና ፓርቲ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሴቶች ሊግ ኃላፊ ከልቱም አሸናፊ ገለጹ።

በብልጽግና ፓርቲ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሴቶች ሊግ አባላት በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳይ ዛሬ በአሶሳ ከተማ ምክክር እያካሄዱ ነው።

May be an image of 1 person and standing

በፓርቲው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሴቶች ሊግ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ከልቱም አሸናፊ ለኢዜአ እንዳሉት በፓርቲው የክልሉ ሊግ አባላት ዛሬ በአሶሳ ውይይት ጀምረዋል።

የውይይቱ ዓላማ ሽብርተኛው ህወሃት ዳግም የከፈተብንን ጦርነት ለመመከት የክልሉ ሴቶች ለሃገር መከላከያ የሚያደርጉትን ድጋፍ እንዲያጠናክሩ ማድረግ ነው ብለዋል።

መንግስት የሠላም አማራጭ የተከተለው የትግራይን ህዝብ ዘላቂ ጥቅም በማሰብ እንደሆነ ጠቁመው ቡድኑ ግን ለሶስተኛ ጊዜ ወረራ መፈጸሙን ተናግረዋል።

የሽብር ቡድኑ በክልሉ መተከል ዞን ያደረሰው ጥፋት ጉዳት ቢያስከትልም ህብረተሰቡ ሠላም ወዳድ በመሆኑ የክልሉ ሰላም ተመልሷል ነው ያሉት ሃላፊዋ።

አሻባሪው ህወሃት ለሠላም የተዘረጋውን የኢትዮጵያ እጅ ነክሶ የጀመረውን የጥፋት ጉዞ ለሠላማችን ዘብ በመቆም እንገታዋለን ብለዋል።

May be an image of 1 person, standing and indoor

በፓርቲው የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ሊግ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ወይዘሮ ዘሐራ ሰላማ በበኩላቸው የከተማው ሴቶች በመስዋእትነት የተገኘው ለውጥ እንዲደናቀፍ አይፈልጉም ሲሉ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም