ሀይማኖት ለሰላም ክልል አቀፍ ኮንፍራንስ በሀዋሳ እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
ሀይማኖት ለሰላም ክልል አቀፍ ኮንፍራንስ በሀዋሳ እየተካሄደ ነው
ሀዋሳ ነሃሴ 23 ቀን 2014 (ኢዜአ) የ“ሃይማኖት ለሰላም” ክልል አቀፍ የሰላም ኮንፍረንስ በሀዋሳ እየተካሄደ ነው።
መድረኩን የኢፌዴሪ ሰላም ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ሲሆን ከደቡብ፣ ሲዳማና ኦሮሚያ ክልሎች የተወከሉ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ የስራ ሃላፊዎችና የሃይማኖት አባቶች እየተሳተፉበት ነው።
መድረኩ ሃይማኖታዊ እሴቶች ለሰላምና ለአብሮነት ያላቸውን ሚና ለማሳደግ ማለሙም ታውቋል።
በክልሎቹ በተለያየ ጊዜ ያጋጠሙ የሰላም መደፍረስን ለመፍታት በተደረገው እንቀስቃሴ የሃይማኖት ተቋማቱ ሚናና ከመንግስት አካላት ጋር የነበራቸው ቁርኝት ላይ ውይይት ይደረጋልም ተብሏል።
የሃይማኖት ተቋማት ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን በሚደረገው ሂደት ውስጥ የሚኖራቸውን ሚና ለማጉላትና ከመንግስት ጋር በመቀራረብ ለሰላምና ለአብሮነት አንዲሰሩ የሚያደርጉ ተመሳሳይ መድረኮች በቀጣይም በተለያዩ ክልሎች እንደሚካሄዱ ተገልጿል።
ለአንድ ቀን በተዘጋጀው መድረክ ሃይማኖት ለሰላም በሚል የተዘጋጀውን ጽሁፍ ጨምሮ ሌሎች ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው ተመላክቷል።
በመድረኩም የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሃፊ ሊቀ ትጉሃን ታጋይ ታደለና የሰላም ሚኒስቴር ተወካይና የሰላም ግንባታ መሪ ስራ አስፈጻሚ ዶክተር አወቀ አጥናፉን ጨምሮ ሌሎች የሚመለከታቸው አካላትም ተገኝተዋል።