ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አሸባሪው ሕወሓት ሕጻናትን በግዳጅ ለውትድርና የመመልመልና የመጠቀም ድርጊት ሊያወግዘው ይገባል- አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ - ኢዜአ አማርኛ
ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አሸባሪው ሕወሓት ሕጻናትን በግዳጅ ለውትድርና የመመልመልና የመጠቀም ድርጊት ሊያወግዘው ይገባል- አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ
ነሐሴ 22 ቀን 2014(ኢዜአ) በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ዓለም አቀፋ ማህበረሰብ አሸባሪው ሕወሓት ሕጻናትን በግዳጅ ለውትድርና በመመልመልና በመጠቀም እየፈጸመ ያለውን ድርጊት እንዲያወግዝ ጠየቁ።
ለሕጻናት ግድ የሚሰጠው ማንኛውም አካል አሸባሪው ቡድን የፈጸመውን ድርጊት በጽኑ ሊኮንነው እንደሚገባ አምባሳደሩ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ ገልጸዋል።