አቶ ኢሳያስ ጅራ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሆነው በድጋሚ ተመረጡ - ኢዜአ አማርኛ
አቶ ኢሳያስ ጅራ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሆነው በድጋሚ ተመረጡ
ነሐሴ 22 ቀን 2014 (ኢዜአ) አቶ ኢሳያስ ጅራ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሆነው በድጋሚ ተመረጡ።
በቀጣይ አራት አመታት ፌዴሬሽኑን ለማገልገል በፕሬዚዳንትነት የተመረጡት አቶ ኢሳያስ ከተፎካካሪዎቻቸው በሰፊ የድምጽ ብልጫ በማግኘት ነው።
አቶ ኢሳያስ ጅራ 94፣ አቶ መላኩ ፈንታ 27 እንዲሁም ኢንጂነር ቶክቻ አለማየሁ 17 ድምጽ አግኝተዋል።