በምንሰራቸው ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ስራዎች የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት እያረጋገጥን መሄድ ግዴታችን ነው- ከንቲባ አዳነች አቤቤ - ኢዜአ አማርኛ
በምንሰራቸው ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ስራዎች የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት እያረጋገጥን መሄድ ግዴታችን ነው- ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ነሐሴ 22 ቀን 2014 (ኢዜአ) በምንሰራቸው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም ፖለቲካዊ ስራዎች የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት እያረጋገጥን መሄድ ሃላፊነታችንም ግዴታችን ነው ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ ፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዛሬው እለት የከተማ አስተዳደሩ የወጣቶች አደባባይ በሚል የሰየመውን ፓርክ ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል፡፡
በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልእክት እንደተናገሩት ኢትዮጵያ የወጣት ሃገር ናት፤ ወጣቶቿ ደግሞ የዛሬም የመጪው ዘመን ተስፋዎቿ ናቸው፡፡
በመሆኑም በከተማዋ የሚከናወኑ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ስራዎች የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማረጋጋጥ ሃላፊነታችንም ግዴታችን ነው ሲሉ ተናግረዋል።
"በአዲስ አበባ በርካታ አደባባዮችን ስናድስና አዳዲስ ስንገነባ ፤በአብዛኛው ስያሜ አላቸው፡፡ በጀግኖች የኢትዮጵያ ልጆች ስም ፤በሴቶች ስም በህፃናት ስም አደባባዮች ያሉ ሲሆን በወጣቶች ስም ግን እስካሁን አልነበረም" ብለዋል፡፡
"ወጣቶች በሃገር ግንባታ ጉልህ ሚና ያላቸው በመሆኑ ከማዘጋጃ ቤት በቅርብ ርቀት በሚገኘው እና መሃል ከተማ ያለውን አደባባይ በእናንተ ስም ሰይመናል ፤ከዛሬ ጀምሮ የእናንተ ነው" ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ ለሰላም የሚተጉ ፤ ለሰላሟ መስዋእትነት የሚከፍሉ ልጆች ያሏት አገር ናት፤ ያሉት ከንቲባ አዳነች ሁሉም ወጣቶች ለሃገራቸው በአንድነት እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡