አምባሳደር ሽፈራው በሱዳን ገዳሪፍ ከተማ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
አምባሳደር ሽፈራው በሱዳን ገዳሪፍ ከተማ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ መስከረም 8/2011 በሱዳን የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሽፈራው ጃርሶ በሱዳን ገዳሪፍ ከተማ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር መወያየታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አመለከተ። የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ አምባሳደሩ በገዳሪፍ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መብት እንዲከበርና ችግሮቻቸው እንዲፈቱ ኤምባሲው ይሰራል። አምባሳደሩ በቆይታቸው ከገዳሪፍ የፖሊስ ኮሚሽንና ከዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ ሃላፊዎች ጋር ባደረጉት ውይይት በአካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን እንዲደግፉ ጠይቀዋል። በካርቱም ከሚገኘው ኤምባሲ በተጨማሪ በገዳሪፍ የኢትዮጵያ ቆንጽላ ጽህፈት ቤት የሚገኝ ሲሆን ይህም በአካባቢው ለሚኖሩ ወገኖች ድጋፍ ያደርጋል።
አምባሳደር ሽፈራው የሹመት ደብዳቤያቸውን ለሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር ሲያቀርቡ የኢትዮጵያና የሱዳን ወዳጅነትና ትብብር ተጠናክሮ እንዲቀጥል በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ መናገራቸው ይታወሳል። ኢትዮጵያ በጥንታዊው የአክሱም ዘመነ መንግሥት ከሱዳኑ የሜሮይ ሥልጣኔ ጋር የነበራትን ታሪካዊ ግንኙነት አሁን ላይ በምጣኔ ኃብትና በፖለቲካው ዘርፍ አዳብራዋለች።