ቀጥታ፡

አሸባሪው ህወሓት ወረራ ፈጽሞባቸው በነበሩ አካባቢዎች ያደረሰው ግፍ ቡድኑ ለሰብዓዊነት ደንታ እንደሌለው በግልጽ ያሳዩ ናቸው

ነሃሴ 20/2014/ኢዜአ/ አሸባሪው ህወሓት ወረራ ፈጽሞባቸው በነበሩ አካባቢዎች ያደረሰው ግፍ ቡድኑ ለሰብዓዊነት ደንታ እንደሌለው በግልጽ ያሳዩ ናቸው።

በተሰጠው የአመራርነት ዘመን ሕዝቡን ከማገልገል ይልቅ በዙሪያው የሰበሰባቸውን ቅጥረኞች ሲያበለጽግ የኖረው አሸባሪው ህወሓት በሕዝብ ብሶት ተገፍቶ ከሥልጣን መባረሩ ይታወቃል፡፡

ቡድኑ መቀሌ መሽጎ የሽብር ሴራ ሲያጠነጥን ከርሞ ጥቅምት 2013 ዓ.ም.በሰሜን እዝ ላይ ጥቃት በመፈጸምና  እንዲሁም ወረራ በፈጸመባቸው የአማራና አፋር ክልሎች ላይ ታሪክ የማይረሳው ግፍ ፈጽሟል፡፡

በዚህም የሽብር ቡድኑ ሰብዓዊነት የማይሰማው ጨካኝ መሆኑን በፈጸማቸው የጭካኔ ተግባሮቹ በይፋ አረጋግጧል።

የአሸባሪው ህወሓት ሰው በላዎች በምጥ የምትጨነቅን  እናት፣ እህት፣ ወይም  ሚስት በጭካኔ ከእነ ፅንሷ ለሞት የሚዳርጉ ናቸው፡፡

የሽብር ቡድኑ በወረራ ይዟቸው በነበሩ የአማራ ክልል አካባቢዎች በፈጸመው ግፍ ሰለባ ከሆኑ እናቶች መካከል ወይዘሮ ዳሳሽ መስፍን የሽብር ቡድኑ አባላት በቤቷ የነበረውን ጥሪቷን አሟጠው ከጨረሱ በኋላ ህፃን ልጇን በጥይት ሩምታ አካለ ጎደሎ አድርገውት መሄዳቸውን በእምባ ታጅበው ይናገራሉ፡፡

አሸባሪው ህወሓት በአፋርና አማራ ክልሎች በሴቶች፣ ህፃናት እና አረጋዊያን ላይ የፈጸመው ጭፍጨፋ፣ አስገድዶ መድፈር እና ሌሎች ፆታዊ ጥቃቶች ለመናገር አይደለም ለመስማት የሚከብዱ ናቸው።

ወላጆቻቸውን የሚጦሩ ወጣቶችን ህይወቴ ከሚሏቸው ቤተሰቦቻቸው ያለምንም ጥፋታቸው በግፍ በመረሸን አዛውንቶችን ለዘላለም ሀዘንና ስቃይ የሚዳርጉ ናቸው የሽብር ቡድኑ ግፈኞች፡፡

ቦሰና ገላው የተባሉ አዛውንት የህወሓት ወራሪዎች  ልጃቸውን በራቸው ላይ በግፍ እንደገደሉባቸው በተሰበረ መንፈስ ውስጥ ሆነው ይናገራሉ፡፡

የህወሓት አሸባሪዎች አንድን ሴት እስከ 15 በመሆን እየተፈራረቁ መድፈር፤ እናት እና ልጅን በአንድ ላይ መድፈር፤ ልጆችን በእናቶቻቸው ፊት መድፈር፤ የስምንት ወር እመጫትን ጨቅላ ልጇን በፈላ ውኃ ዉስጥ እንጨምራለን በማለት እናትዋን በማስፈራራት በመድፈር ነውረኛነታቸውን በአደባባይ አሳይተዋል፡፡

ከእነዚህ ሰለባዎች አንዷ የሆነችው ሴት "በቡድን በመፈራረቅ ደፈሩኝ፤ ለሰው የማልናገረውን ቁስል ትተውልኝ ሄዱ" ስትል የቡድኑን ግፍ ትናገራለች፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም