ቀጥታ፡

ካናዳ በኢትዮጵያ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል የተጀመረውን እንቅስቃሴ ትደግፋለች

ነሐሴ 20 ቀን 2014 (ኢዜአ) የካናዳ መንግስት በኢትዮጵያ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል የተጀመረውን እንቅስቃሴ እንደሚደግፍ ገለፀ ።

የትምህርት ሚኒሰትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኢትዮጵያ የካናዳ መንግስት አምባሳደር ከሆኑት ሚስተር ስቴፋኒ ጆቢን ጋር በትንትናው ዕለት ተወያይተዋል።

የካናዳ አምባሳደር በኢትዮጵያ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል የተጀመረውን እንቅስቃሴ አድንቀው ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል።

በኢትዮጵያ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎች ላይ ውይይት አካሂደዋል።

የእንግሊዝኛ ቋንቋ ማሻሻያ መርሃ-ግብርን ተግባራዊ ለማድረግ የካናዳ መንግስት ስለሚያደርገው ድጋፍ እና የበጎ ፈቃደኞች መምህራን ስምሪት ላይ ውይይት ተደርጓል።

የእንግሊዝኛ ቋንቋ ማሻሻያ መርሃግብር ለማሳካትም በኤምባሲያቸው በኩል፣ በካናዳ ዓለምአቀፍ የልማት ትብብር ሚኒስቴር እና የካናዳ ዩኒቨርሲቲዎች አማካይነት እና በኦታዋ ከተቋቋመው የኢትዮጵያ ግብረሃይል ጋር በመነጋገር እና በማስተባበር የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡም አምባሳደሩ ቃል ገብተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም