የኢትዮጵያ አየር መንገድ "በአፍሪካ ተመራጭ አየር መንገድ” ሽልማት አሸናፊ ሆነ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ "በአፍሪካ ተመራጭ አየር መንገድ” ሽልማት አሸናፊ ሆነ
ነሐሴ 20 ቀን 2014 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የግሎባል ትራቭል መጽሔት ባዘጋጀው የ2022 የትራዚስ አዋርድ ዳሰሳ “በአፍሪካ ተመራጭ አየር መንገድ” አሸናፊ ሆኗል።
አየር መንገዱ በውድድሩ ድምጽ የማሰባሰብ ሂደት አሸናፊ የሚያደርገውን ድምጽ አግኘቷል።
አየር መንገዱ በአፍሪካ ተመራጭ አየር መንገድ ሆነን በደንበኞቻችን በመመረጣችን በጣም ኩራት ይሰማናል ብሏል።