ለህግ የበላይነትና ለዜጎች ሰብዓዊ መብት መከበር ህዝቡ በአንድነት ሊሰራ ይገባል...አቶ ኡቦንግ ሜቶ - ኢዜአ አማርኛ
ለህግ የበላይነትና ለዜጎች ሰብዓዊ መብት መከበር ህዝቡ በአንድነት ሊሰራ ይገባል...አቶ ኡቦንግ ሜቶ
ጋምቤላ መስከረም 8/2011 የህግ የበላይነት እንዲከበርና የዜጎች መብት የተረጋገጠበት ሀገር ለመፍጠር ህዝቡ በአንድነት ሊሰራ እንደሚገባ የአዲስቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦቦንግ ሜቶ ገለጹ። በክልሉ በ1996 ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ህይወታቸው ያለፉትን ዜጎች በማሰብ የነበረውን ጥላቻና ቂም በመሻር በጋምቤላ ከተማ የእርቅ መርሃ-ግብር ተካሂዷል። የንቅናቄው ዋና ዳያሬክተር አቶ ኦቦንግ ሜቶ በመረሃ-ግብሩ ላይ እንደተናገሩት በቀልንና ጥላቻን በመሻር በሀገሪቱ የተጀመረውን ለውጥ ውጤታማ ለማድረግ ሁሉም ዜጋ የድርሻውን ሊወጣ ይገባል። “በተለይም የብሄር የበላይነት ሳይሆን የህግ የበላይነት፣የዜጎች እኩልነትና ሰብዓዊ መብቶች የተከበሩባት ክልልና ሀገር ለመፍጠር ሁሉም በአንድነት ተባብሮ ሊሰራ ይገባል” ብለዋል። እንደ ሃገር የመጣውን ለውጥ ውጤታማ ለማድረግ የክልሉ
ህዝብ በተለይም ወጣቱ ከሌሎች ኢትዮጵያዊ ወንድሞቹ ጋር በአንድነት ተባብሮ ሊሰራ እንደሚገባም አስገንዝበዋል። ''ወደ ክልሉ የመጣሁት ዘር ወይም ብሄር ለመፈለግ ሳይሆን የዜጎችን የሰብዓዊ መብቶችና የህዝቦችን የአንድነትና አብሮነት እንዲጠናከር በማሰብ ነው'' ሲሉ ተናግረዋል። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሰናይ አኩዎር በዚሁ ጊዜ “በክልሉ ብሎም የሀገሪቷ በአፄዎቹ ስርዓት ወቅትም ቢሆን ህዝቡ በአንድነት አብሮ የመኖር ታላቅ እሴትና ታሪክ አለው” ብለዋል። በመሆኑም የክልሉ ህዝብ በተለይም ወጣቱ ይህን የቆየ እሴቱን በመጠበቅ ለክልሉና ለሀገሪቱ ሁለንተናዊ ለውጥ አንድነቱን ጠብቆ በጋራ መስራት እንዳለበት አሳስበዋል። የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳሬክተር አቶ ኦቦንግ ሜቶ የሚመራው ቡድን የክልሉ ህዝቦች አንድነት ኢንዲጠናከር ለጀመሯቸው ስራዎች አድናቆታቸውን ችረዋል።
ዳልዲም በሚል ስያሜ የተደራጁ ወጣቶች በመረሃ ግብሩ ማጠናቀቂያ ላይ ባወጡት የአቋም መግለጫ ከሌሎች የኢትዮጵያ ወንድሞቻቸው ጋር በመሆን ሀገራዊ ለውጡን ውጤታማ ለማድረግ እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል ። ብሄርተኝነት፣ ጎሰኝነት፣ ሙስናና ኪራይ ሰብሳቢነት አዲሱን ሀገራዊ ለውጥ የሚጎትቱ በመሆናቸው አጥብቀው ለመታገል መዘጋጀታቸውንም ገልጸዋል። በስነ-ስርዓቱ ላይ የክልሉን ከፍተኛ አመራሮች ጨምሮ የከተማው ነዋሪዎችና ወጣቶች ታዳሚዎች ነበሩ።