ቀጥታ፡

ውድመትና ዘረፋ በተካሄደበት ማግስት የአሸንድየ በአልን በላስታ ላልይበላ በደመቀ ሁኔታ ማክበር የአይበገሬነት ማሳያ ነው

ነሐሴ 18 ቀን 2014 (ኢዜአ)የላልይበላ ህዝብ በአሸባሪው የህወሃት ቡድን ውድመትና ዘረፋ በተካሄደበት ማግስት የአሸንድየ በአልን እንዲህ በደመቀ ሁኔታ ማክበር መቻሉ የአይበገሬነት ማሳያ መሆኑን የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ ገለፁ።

ርዕሰ መስተዳድሩ የላስታ ላልይበላ የአሸንድየ በአልን ምክንያት በማድረግ ከአጋር አካላትና ከህብረተሰብ ክፍሎች ጋር የፓናል ውይይት አካሂደዋል።በውይይቱም ነዋሪዎች በከተማዋና አካባቢዋ የሚስተዋሉ የመሰረተ ልማት ችግሮች እንዲቀረፉላቸው ጠይቀዋል።

በቱሪዝም መስህብነታቸው በአለም ዙሪያ የሚታወቁት ቅርሶች ከረጅም ጊዜ በፊት የተቆረቆሩ በመሆናቸው ለመፍረስና መሰንጠቅ አደጋ መጋለጣቸውን ገልጸዋል።

ርእሰ መስተዳድሩ የላልይበላ ህዝብ የወራሪ ሃይሉ ወቅት ክፉ ጊዜን በጥበብ ማለፍ መቻሉና የአሸንድየ በአልን እንዲህ በደማቅ ሁኔታ ማክበር በችግሮች ሊበገር እንደማይችል ማሳያ ነው ብለዋል።

May be an image of 7 people, people standing and outdoors

በላልይበላና አካባቢው የልማትና የቱሪዝም እንቅስቃሴ ላይ ችግሮች መኖራቸውን ገልፀው፤ መፍትሄው ላይ የሚደረገው የጋራ ርብርብ ይጠበቃል ነው ያሉት።

በሌላ በኩል ጉዳት የደረሰባቸው ቅርሶች ተገቢውን እድሳት እንደሚያገኙ በመጥቀስ ከወዲሁ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጀመራቸውን የገለጹት የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው ናቸው።

May be an image of 3 people and people standing

በመድረኩ የላልይበላ ከተማ ያለችበት ወቅታዊ ሁኔታ እና የመፍትሄ አቅጣጫን የሚያመላክቱ ሁለት የጥናት ፅሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

በመድረኩ የቱሪዝም ሚኒስትሯ ናኒሴ ጫሊን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም