በባለልዩ ጣዕም የቡና ቅምሻ አንድ ኪሎ የኢትዮጵያ ቡና በ47 ሺህ 236 ብር ተሸጠ - ኢዜአ አማርኛ
በባለልዩ ጣዕም የቡና ቅምሻ አንድ ኪሎ የኢትዮጵያ ቡና በ47 ሺህ 236 ብር ተሸጠ
ነሐሴ 18 ቀን 2014 (ኢዜአ) በኢትዮጵያ ለሦስተኛ ጊዜ ሲካሄድ የቆየው የባለልዩ ጣዕም የቡና ቅምሻ (ካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ) ውድድር የኢትዮጵያ ቡና አሸነፈ፡፡
የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን “ቡናችን ዳግም አሸነፈ፤ አርሶ አደሮቻችንም አሸንፈው የኢትዮጵያ ኩራት ሆነዋል” ብሏል፡፡
በዘንድሮው የባለልዩ ጣዕም የቡና ቅምሻ 2022 ውድድር ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ በጥራቱ በአንደኝነት ከፍተኛ ነጥብ መመዝገቡን ባለስልጣኑ አስታውቋል፡፡
ከትናንትና ምሽት ጀምሮ በተከናወነው ዓለም ዓቀፍ ኦንላይን ጨረታ እጅግ በሚያስደንቅ ሁኔታ አንድ ኪሎ ግራም ቡና 884 ነጥብ 10 ዶላር ወይም 47 ሺህ 236 ነጥብ 23 ብር ተሸጧል ነው ያለው፡፡
ይህ ዋጋ ለአንድ የኢትዮጵያ ቡና የተሰጠ አስደናቂ ዋጋ መሆኑን የባለስልጣኑ መረጃ አመላክቷል፡፡
ይህ ስኬት እንዲመዘገብ ላስቻሉ ሁሉም አካላት ባለስልጣኑ አመስግኗል፡፡